Saturday, July 15, 2017

#Oromo#Oromiya

አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል እንደሚባለው ወያኔ እስከዛሬ የዘረፈው አልበቃ ብሎት በነጋዴው ማህበረሰብ ላይ 10 እጥፍ የግብር ጭማሪ ለማድረግ እየሞከረ ነው። ይህ ጭማሪ ምንም አሳማኝ ምክንያት የለውም። ባለፈው አመት ሀገሪቷ በፖሊቲካ ቀውስ ስትታመስ እንደነበረች ሁሉም ያውቃል። ያ ቀውስ የንግድ እንስቃሴን ክፉኛ ጎድቷል። ተቃውሞው መንገዶችን እየዘጋ የንግድ እንክስቃሴን ያወከ ሲሆን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የንግድ ቤቶች ሳይመሽ እንዲዘጉ በማድረግ እና ሁለገብ እንቅሳቅሴን በማስተጓጎል የነጋዴውን ገቢ ክፉኛ ጎድቷል። እናም የነጋዴው ገቢ በመቀነሱ ዘንድሮ ግብር ይቀንሳል ተብሎ ነበር የተጠበቀው። በብዙ እጥፍ ማሳደጉ ማንም ያልጠበቀው ምንም ኢኮኖሚያዊ አመከንዮ የሌለው ነው። እናም የነጋዴው ማህበረሰብ ይህን ምክንያታዊ ያል ሆነ ጭማሪ እምቢ የማለት ህጋዊ እና ሞራላዊ አውነት አለው። መንግስት በግድ አስከፍላለሁ ካለ ሌላውን ህብረተሰብ ያሳተፈ ከፍተኛ ተቃውሞ ይጠብቀዋል። በኦሮሚያ ተቃውሞዎች ከወዲሁ ጀምረዋል። በአምቦ፣ ጉደር እንዲሁም በምስራቅ ሀረርጌ ነጋዴዎች በቅዳሜ የገበያ ቀን ሱቆቻቸውን በመዝጋት እምቢተኝነታቸውን እየገልጹ ነው። እናም መንግስት ተብዬው ቆም ብሎ ሊያስብበት ይገባል። ዘንድሮ ነጋዴው ልክ ያአምናውን ያክል ግብር እንዲከፍል ይደረግ። የ 1% ጭማሪም ተቀባይነት የለውም።

No comments: