Thursday, October 15, 2020

#AbiyMustGo#OromoProtests#Ethiopia

በ Henok Dejene

 በኩቡር ጃል ዳዎድ ኢብሳ ቤት የነበረን የሶስት ቀን እገታና የአንድ ቀን የፖሊስ ጣቢያ ቆይታችን!
______________________
የኦነግ ሊቀመንበርነት ጃል ዳዎድ ኢብሳ መግለጫ በሚሰጥበት ቦታ ከ3 ከጓደኞቼ ጋር ተገኝተን ነበር። የሆነው ነገር እጅግ በጣም ያሳፍራል።መጀመሪያ የክብር ጃል ዳዎድ ኢብሳ መኖሪያ ቤት ገና እንደደረስን ካሳቸው ቤት አጠገብ  የአፍሪካ ፕሬዝዳንት መኖሪያ ግቢ አካባቢ ለጥበቃ የቆሙ የሚመስሉ የፌዴራል ፖሊሶች ተደርድረው ነበር።በቦታው አንጋፋ ሰዎችና የተለያዩ እንግዳዎች ተገኝተዋል።የሆነው ሆኖ ፕሮግራሙ ተጀመረ! ፕሮግራሙ እንደተጀመረ ሀያ ደቂቃ እንደሞላው የግቢው በር ተንኳኳ! በሩ እንደተከፈተ አራት የፌደራል ፖሊስ እና አንድ ሸሚዝ የለበሰ የደህንነት ሰው ግቢ ውስጥ ካልገባን ሲሉ ፤በሩን የከፈቱት ቄሮዎች የፍርድቤት ማዘዣ ካልያዛችሁ መግባት እንደማይችሉና ህጉም እንደማይፈቅድላቸው አስረዷቸው። ነገር ግን ቃል በቃል ወታደሮቹ የመለሱት  መልስ ሊያውም በንቀትና በአማርኛ "ውስጥ ለመግባት የፍርድ ቤት ትእዛዝ አያስፈልገንም!" በማለት መሳሪያ አቀባብሎ ዞር በል! እያሉ ወታደሮቹ ግርግር ፈርጥረው ፕሮግራሙን ሲረብሹ ክቡር ጄል ዳዎድ ኢብሳ መግለጫ መስጠቱን አቋርጠው ወጥተው ሲያናግሯቸው በአንዴ ወታደሮቹ ስክን አሉ። ባህሪያቸው ለምን በአንድ ከያዙን ልቀቁኝ ወደ መስከን እንደተቀየረ አልገባኝም።
....ንግግር ተጀመረ! ወታደሮቹ እኛ የመጣነው ጋዜጠኞቹን ፈልገን ነው። እነሱን አሶጡልን አሉ! በትዛዛቸውም መሰረት ነገሮቹን ላለማባባስ ሲባል ጋዜጠኞቹ ወጡ ተያዙ፤ ቀጠሉና ፕሮግራሙ ላይ የነበሩትን ሰዎች ስም እንመዝግብ አሉ! ፕሮግራሙ ላይ ያሉትን መዘገቡ ለግዜው ማንም ከግቢው ወጥቶ እንዳይሄድ ከላይ የተሰጠን ትዛዝ ስላለ ማንም መግባት መውጣት አይችልም። ከግቢ የምትወጡት ትዛዙ በድጋሚ ከላይ ሲሰጠን ነው ተብለን ተቀምጠን። ሰዓታት አለፉ! ጠበቅን መጠበቅን የተለየ ነገር የለም  እዛው ቤት አደርን። 

በንጋታው በጠዋት ተጨማሪ ወታደሮች የጃል ዳዎድ ኢብሳ መኖሪያ ግቢ ከበው ይገኛሉ።  እንግዶቹ አሁንም ድረስ እንደታገቱ ነው። ወደ ወስጥ ማንም አይገባም። ወደ ውጪም ማንም አይወጣም። 

ከጠዋቱ አራት ስዓት ላይ የጃል ዳዎድ ኢብሳ እንግዶች ከግቢ ወጥተው መሄድ እንደሚችሉ ትዛዝ ከበላይ መጣ ተባለ። እንግዶቹም ከወጡ በኃላ በፖሊስ መኪና ልክ ወንጀል እንደሰራ ሰው ተጭነው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄዱ። በቤቱ ውስጥ የቀረነውም ላለመውጣት ወሰንን። 

የእንግዶቹ እና የጋዜጠኞቹ መታስርና ከተለያዩ ከሀገር ውስጥ ሚዲያዎች አልፎ ወደ አለም አቀፍ Human rights ተቋማት ጉዳዩ ደረሰ። የሆነው ሆኖ  በስንት ሙግት ወደ ማክሰኞ አመሻሻ ላይ ጋዜጠኞቹም የጃል ዳዎድ  እንግዳዎቹም ከእስር ተለቀቁ። በንጋታው ዕሮብ እለት ጃል ዳዎድ ቤት ውስጥ ቀርተን የነበርን ሁሉ ከሁለት ቀን  የጃል ዳዎድ ቤት እገታ በኋላ አንድ ቀን  ፖሊስ ጣቢያ አሽተው  አንገላተው ለቀቁን።
_______________
በጃል ዳዎድ ቤት በነበርን ቆይታ አንድም እንከን ሳይገጥመን ሁሉነገር ተሟልቶልን ሳንጨናነቅ በክቡር ጄል ዳዎድ ኢብሳ መኖሪያ ቤት በማሳላፋችን እጅግ በጣም ታላቅ ክብርና ደስታ ለታላቁ አንጋፋው የኦሮሞ ህዝብ ትግል አባት ምስጋና ማቅረብ እንፈልጋለን።🙏

No comments: