Friday, August 18, 2017

#OromoProtests

ማስታወቂያ
*********

በቀጣዩ ሳምንት ሰኞ እና ማክሰኞ ማለትም ነሃሴ 15 እና 16 በመላው ኦሮሚያ ከቤት ያለመውጣት የተቃውሞ አድማ በቄሮዎች ተጠርቷል። አድማው በነጋዴው ላይ ከአቅም በላይ የተጣለው ግብር እንዲነሳ፤ መሪዎችን ጫምሮ የፖሊቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እንዲሁም በምስራቅ ኦሮሚያ የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ በህዝቡ ላይ የሚያደርሰው ወረራ እንዲቆም ለመጠየቅ የታቀደ ነው። በዚህ አድማ ህዝቡ ከቤቱ ሳይወጣ በሰላም ተቃውሞውን ያሰማል። ሱቆች አይከፈቱም፤ የትራንስፖርት አገልግሎት አይኖርም፤ የመንግስትም ሆነ የግል ሰራተኞች ስራ አይገቡም። ስለሆነም ህዝቡ አስቀድሞ ለሁለት ቀናት ቤት ለመዋል የሚያስችለውን ዝግጅት ከወዲሁ እንዲያደርግ የየአካባቢው የቄሮ አስተባባሪዎች ጥሪ አድርገዋል። በተጠቀሱት ቀናት የጉዞ እቅድ ያላቹ ሁሉ እቅዳቹን ከወዲሁ እንድትከልሱና እንድታስተካክሉ አስተባባሪዎቹ መክረዋል።

ይህንን አድማ ጥሰው በሚንቀሳቀሱት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰዱ የአድማው አስተባባሪ ቄሮዎች ቡድን አስጠንቅቋል።

No comments: