ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ አመፅ አስመልክቶ ከኦሮሞ ቄሮ ለነፃነት ድርጅት የተሰጠ አጭር መግለጫ
==========================================
ጭካኔን የተሞላው መላው የኦሮሞ ህዝብ ያስደነገጠና መሪር ሃዘን ውስጥ የከተተው የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መገደል በአገር ውስጥና በውጭ ሃገራት የሚኖሩትን የኦሮሞ ቄሮ ለነፃነት ታጋዮችን ይህ ነው የማይባል አቻ የሌለው ሃዘን ውስጥ መክተቱ ይታወቃል::
የኦሮሞ የአይን ብሌን የሆነው የሃጫሉ ሁንዴሳን መሰዋት ሰበብ በማድረግ የኦሮሞን ህዝብ ትግል አቅጣጫ ለማሳትና የኦሮሞን ህዝብ ሊወጣው ወደማይችለው የባርነት አዘቅት ውስጥ ለማስገባት እንደ ፖለቲካ መሳሪያነት እየተገለገሉበት መሆኑን እየተካሄደ ያለው የወቅቱ አካሄድ በግልፅ ያሳያል:: በሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም በተፈፀመው ከጀግናው አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ ያለውን ሁኔታ መንግስት ነፃና ገለልተኛ በሆነ አካል አስመርምሮ ለኦሮሞ ህዝብና ለመላው የአለም ህዝቦች እንዲገልፅ የተጠየቀ ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ ምንም ምላሽ ያልተሰጠበትና ይልቁንም ሃላፊነት በጎደለው መልኩ የመንግስት ባለስልጣናትና ሃላፊዎች ለፕሮፖጋንዳነት እየተጠቀሙበት ያሉ ሲሆን በተቃዋሚ የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶች ላይ በሚዲያዎቻቸው አማካኝነት የማሸማቀቅ ዘመቻ ከፍተዋል::
ቄሮ ለነፃነት (Qeerroo Bilisummaa) አርቲስቱ ከተሰዋበት ከስርኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም አንስቶ በሁሉም የኦሮሚያ ክፍሎች ውስጥ በተቀናጀና ጀግንነት በተሞላ መልኩ እምቢተኝነቱንና ለኦሮሞ ህዝብ በቁርጠኝነት መፋለሙን ቀጥሎበታል:: በየወረዳና በየቀበሌውም ውስጥ ከፍተኛ መስዋዕትነት እየተከፈለ ይገኛል:: በአንፃሩ ይሄ መንግስት ሆን ብሎ ኦሮሚያን የጦርነትና የረብሻ አውድማ በማድረግ ህዝቡ እንዳይረጋጋ እያደረገ ይገኛል::
የአገር መከላከያ ሰራዊት ሃላፊነት በማይሰማው መልኩ በየከተማውና በየገጠሩ ህዝቡን እየዘረፈና እየገደለ ማሰቃየቱን የእለት ተእለት ተግባሩ አድርጎታል:: እስራት ስቃይና ህዝብ ወደ ጫካ መሸሽ በሁሉም የኦሮሚያ ክፍሎች ውስጥ የተለመደ ሆኗል:: ይህ ድርጊት መፍትሄ ከማጣቱ የተነሳ የኦሮሞ ቄሮና ቀሬ ቀደም ብሎ ዘርግቶት ባለው መዋቅሩ በመታገዝ ስር ነቀል ለውጥንና የኦሮሞን ህዝብ ድል ሙሉ በሙሉ ለማስከበር መራራ ትግል ለማድረግ በሁሉም የኦሮሚያ ከተሞች ውስጥ የባርነት እምቢተኝነት አመፅ (Fincila Diddaa Gabrummaa) እያካሄደ ይገኛል:: ይህ ነው የማይባል መስዋዕትነት እየከፈለም ነው::
ኢንተርኔት ከማቋረጡ ጋር ተያይዞ መንግስት የኦሮሞ ቄሮ ለነፃነት ሆነ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን በሙሉ የሚያወጧቸውን መግለጫዎንም ሆነ ድምፃቸውን ለአለም ህዝቦች እንዳያሰሙ ችግር ፈጥሯል:: በየቦታው እየተደረገ ያለውን የኦሮሞን ህዝብ የዕንቢተኝነት ትግል እስራትና ግድያ እስከ አሁን መዘገብ በጭራሽ አልተቻለም:: በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያለን ህዝብ ድምፁን አፍነው እየገደሉና እስር ቤት እያጎሩ ማሰቃየትን ሆን ብለው ቀጥለውበታል::
ከሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በተገኘው መረጃ (data) መሰረት ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞን የደረሰው እንደሚገልፀው እስከ አሁን ድረስ በሰላማዊ መንገድ ሃዘኑን ሊገልፅ ከወጣው ህዝብ መሃከል 482 ሰዎች በመንግስ ታጣቂ ሃይሎች ሲገደሉ ከ7000 በላይ የሚሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ታፍነው የደረሱበት አልታወቀም:: ይህ ከሁሉም ኦሮሚያ አካባቢ የተሰበሰበ ዘገባ እንደሚጠቁመው ከሞቱት ሌላ 1300 ሰዎች ቆስለዋል:: የቆሰሉትም ሰዎች ህክምና እንዳያገኙ ተከልክለው አብዛኞቻቸው የሚሞቱበትን ቀን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ::
ይህ ሁሉ መስዋእትነት ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞን ከትግሉ ወደሗላ አልመለሰውም:: ሊመልሰውም አይችልም:: የተማከለው የኦሮሞ ህዝብ ትግል በቄሮ ለነፃነት ድርጅትና ለኦሮሞ ህዝብ ሃቅ በሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅቶች መሪነት ቀጥሎበታል:: ትግሉ ከግብ እስከሚደርስ ድረስ የእምቢተኝነት ትግሉ (FDG) በከተማ ውስጥም ሆነ በገጠር ውስጥ የሚካሄድና ለአንድ አፍታም ቢሆን የማይቆም መሆኑን ለህዝባችን ለማረጋገጥ እንፈልጋለን:: የቄሮ ለነፃነት ትግል መዋቅር ከቀድሞው በበለጠ እጅግ ተጠናክሮ ሰፍቶ በሰከነና ሙያዊ ብቃትን የተካነ እቅድ አውጥቶ ከኮለኔል አብይ አህመድ ጀርባ መሽጎየኦሮሞን ህዝብ ሊጫን እያለመ ያለውን አሮጌውን ጨቋኝ ስርአት ተነቅሎ ግብዓተ መሬቱ እስኪፈፀም ድረስ በቁርጠኝነት ትግሉን የምንቀጥልበት መሆኑን እናረጋግጣለን::
በአሁን ሰዓት ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መሰዋት ጋር በማያያዝ በኦሮሚያና በኦሮሞ ህዝብ ላይ ተከፍቶ ያለው ዘመቻ ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል::
1. በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከውጭ ወደ አገር ውስጥ የገቡትን የኦሮሞ ድርጅት መሪዎችና አባላትን ማሰር
2. የተቃዋሚ ድርጅቶች ቢሮና ንብረት የሆኑትን በሙሉ በመዝረፍ ቢሮውን መዝጋት
3. በኦሮሞ ስም የተቋቋሙ ሚዲያዎችን እንደ OMN, ONN እና የቄሮ ድምፅ (SQ) ያሉት ላይ በመዝመት እንዳይዘግቡ መከልከል እንዲሁም ጋዜጠኛን ማሰር
4. የኦሮሞ ቄሮ ለነፃነት ትግልን ለመግታት ሲባል በከተማና በገጠር ውስጥ አፋን ኦሮሞን የማይችሉ ባህሉን ጨርሰው የማያውቁ እንዲሁም ለኦሮሞ ህዝብ ይህ ነው የማይባል ጥላቻ አላቸው ብለው የሚያስቡትን ከሌሎች አጎራባች ክልሎች አምጥተው ኦሮሚያ ውስጥ በማሰማራት ህዝቡን ማስደብደብና ማስገደል
5. የህዝብ አገልግሎት ሰጪ የሆኑትን ሁሉ እንደ መብራት ዉሃ መንገድና ትራንስፖርት የመሳሰሉትን ማቋረጥ የግልና የመንግስት የህክምና ተቋማትን መዝጋት
6. በመላው አገሪቷ የኢንተርኔት አገልግሎት በማቋረጥ ማንኛውም መረጃ በአገሪቷ ውስጥ እንዳይሰማና ወደ ውጭም እንዳይወጣ እንዲሁም ማንኛውም ዓይነት የመረጃ ልውውጥ እንዳይደረግ በር መዝጋት
7. በሁሉም ኦሮሚያ ዞኖች ውስጥ የሚገኙትን የሃይማኖት አባቶች መምህራንና በየአካባቢያቸው የተከበሩ አዛውንቶችን በማስፈራራትና በማሸማቀቅ እስር ቤት ማጎር የመሳሰሉትን በኦሮሞ ህዝብ ላይ እያደረሱ ነው::
የብልፅግና መንግስት በአሁኑ ሰዓት በአገሪቷ ውስጥ ያለው ችግር በጎሳና በጎሳ መካከል እንደተፈጠረ በማስመሰል በሚዲያና በካድሬዎቹ አማካኝነት የፖለቲካ ንግድ በማካሄድ ላይ ይገኛል:: ቄሮ ለኦሮሚያ ነፃነት ሲል የሚያካሄደው ትግል ማንኛውንም ብሄር የማይነካና ማንንም በጠላትነት ፈርጆ የሚታገል ሳይሆን የተዳፈነውን የኦሮሞ ህዝብ ሃቅ ማስመለስ ብቻ ላይ ያለመ ነው:: የቄሮ ትግል የኦሮሞን ህዝብ መብት እውን ከማድረግ የዘለለ ሌላ የፖለቲካ ተልዕኮ እንዳሌለው ለዘመናት ሲያደርገው የነበረው እንቅስቃሴ ምስክር ነው:: ስለሆነም በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገራት የሚኖረው ህዝባችን እንደ አለፉት አመታት ሁሉ ካለ አንዳች መነጣጠል የኦሮሞ ነፃነት ትግልን ከግብ ለማድረስ የኦሮሞ ቄሮ ለነፃነት ትግልን እንዲያበርርታታ ስንል መልእክታችንን እናስተላልፋለን::
የብልፅግና መንግስት የኦሮሞ የሰጠውን እድልና ያለውን እድል ትዕግስት በመናቅ ህዝባችን በአለም ህዝቦች ፊት እንዲዋረድ በማድረግ ለኦሮሞ ህዝብና የፖለቲካ ድርጅቶች ያለውን ንቀት በግልፅ አሳይተዋል:: የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅት አመራሮችን በማናለብኝነት በማሰር በማሰቃየትና በያዙት ሚዲያዎቻቸው ላይ በማውገዝና ያለ ምንም ማስረጃ ስማቸውን ማጉደፍ የንቀታቸው ማሳያ ነው::
የኦሮሞ ህዝብ እንደ አይኑ ብሌን የሚያያቸው አመራሮቹን መናቅ የኦሮሞን ህዝብ መናቅ ነው:: የኦሮሞ ህዝብ ተስፋ የሆኑትን አመራሮች ማቅለልና አስሮ ማሰቃየት የኦሮሞን ህዝብ መጥላት ነው:: ይህንን ሁኔታ እንዲቀየር ለማድረግ ያለን ብቸኛ አማራጭ አንድና አንድ ብቻ ነው:: በግልፅ አነጋገር እንደተለመደው የነፃነት ትግላችንን በማፋፋም ጭቆናን ከስር መሰረቱ ነቅለን ጥለን ህዝባችንን የነፃነትና የዲሞክራሲን ብርሃን ማጎናፀፍ ነው::
ከዚህ ግርጌ የተዘረዘሩትን አንድ በአንድ እራሱን ብልፅግና ብሎ የሚጠራውና በኮሎኔል አብይ መሐመድ የሚመራው መንግስት በአስቸኳይ ካልተገበረ አሁን በአገሪቷ ውስጥ የተቀጣጠለው እሳት የማይበርድ መሆኑን ቄሮ ለነፃነት ያስጠነቅቃል::
1. በተወዳጁና ብርቅዬው አርቲስታችን ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ የተፈፀመው ግድያ ከመንግስት ነፃና ገለልተኛ በሆነ አካል ተመርምሮና ተጣርቶ ዉጤቱን ለህዝብ እንዲገልፅ:: ይህንን ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦችንም ሆነ ከጀርባው ሆነው ያስፈፀሙ አካላትን ለህግ እልዲያቀርቡ
2. ጠቅላይ ሚኒስቴር ኮሎኔል አብይ አህመድ በአስቸኳይ ስልጣኑን እንዲለቅ:: የፒፒ የስልጣን ዘመን ስላበቃለት ፈርሶ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም
3. በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ግድያና እስራት በአስቸኳይ እንዲቆም::
4. የኦሮሞ ነፃነት ግምባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራሮችን ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ
5. የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ለማደን አሰሳ በማድረግ ሰበብ ምዕራብ ሰሜንና ደቡብ ኦሮሚያን ወሮ ሰላማዊውን ህዝብ ሰላም በመንሳት እያሰቃየ ያለው መከላከያ ሰራዊት ኦሮሚያን ለቆ ወጥቶ ወደመጣበት እንዲመለስ:: የኦሮሞ ህዝብና የኦሮሚያ ሰላም ከኦሮሞ ህዝብ ተወልደው ለህዝባቸው ታማኝና ተቆርቋሪ በሆኑ ፖሊስ አባላት እንዲጠበቅ::
6. የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ነህ ተብለው ለተገደሉና ለአካል ጉዳት ለተዳረጉ አካላት ተገቢ ካሳ እንዲሰጣቸው::
7. ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ተገቢ ውይይት በማድረግ ቋሚ ፕሮግራም ተነድፎ ነፃና ፍትሃዊ የሆነ ምርጫ እንዲደረግ
8. ማንኛውም የህዝብ መገናኛ ሚዲያ እንደ ኢንተርኔት ስልክ እና መብራት የመሳሱሉት እንዲለቀዉ
9. የኦሮሞ ነፃ ሚዲያዎች እንደ OMN እና ONN ያሉት በአስቸኳይ ስራ እንዲጀምሩ:: ጋዜጠኞቻቸውም ከእስር እንዲለቀቁ:: ከየቢሯቸው የተዘረፉት የሚዲያ መሳሪያዎች እንዲመለሱ
10. የአገሪቱ የወደፊት እጣ ፈንታና ጉዟችን ወዴት ነው የሚለው ሁሉንም የተቃዋሚ ድርጅቶችን ያቀፈ ሆኖ ብልፅግና ለብቻው የግሉ አድርጎ የያዘውን ስልጣን እንዲያበቃ ማድረግ
ከዚህ በላይ የተቀመጡት ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ የማያገኙ ከሆነ ቄሮ ለነፃነት እንደካሁን ቀደሙ ሁሉ በኦሮሚያ ውስጥ የተጀመረውን ትግል በማስቀጠል የኦሮሞን ህዝብ የአገሩ ባለቤት የምናደርግ መሆኑን አፅንተን እናስታውቃለን::
በመጨረሻም መላው የኦሮሞ ህዝብ ከአገር ውጭና በአገር ውስጥ ሆኖችሁ ከአባቶቻችሁ እንዲሁም ከኦሮሞ ህዝብ ትግል በወረሳችሁትን ጀግንነት ሳታቋርጡ ቀጣይነት ባለው መልኩ ለነፃነታችሁ እየታገላችሁ ያላችሁ መሆኑን እያየን ያለን ስለሆነ ለእናንተ ታላቅ ክብር አለን:: እንደቀድሟችሁ ሁሉ አንድነታችሁን አጠንክሩ:: አትከፋፈሉ:: ያለ አንዳች የፖለቲካ ልዩነት ትግላችን ወደፊት ከቀጠለ ሃቃችንን በመዳፋችን ውስጥ የምናስገባበት ቅርብ መሆኑን ልናበስራችሁ እንወዳለን:: የቄሮ ለነፃነት ትግል አመራር በመላው ኦሮሚያ ዉስጥ መንግስትን ማነቃነቅና ትግሉን በፅናት ማስቀጠል የሚያስችል በቂ አቅም እንዳለው እናረጋግጥላችሗለን:: ቄሮ ብሩህ የሆነ ዓላማን በመያዝ በሳልና ጨዋነትን በተሞላ እቅድ ይታገዛል:: በቀላሉ ጠላት የማይበግረው የረጋ መዋቅር አለው:: ድርጅታችን ያወጣውን እቅድና የመታገያ ዘዴን በመጠቀም የኦሮሞን ህዝብ በማሰቃየት ላይ ያለውን ጨቋኝ መንግስት እንደሚያንበረክክ ምንም ጥርጣሬ የለንም:: በውጭ አገራትም ሆነ በአገር ውስጥ የምትገኙ ወገኖች ሁሉ የብልፅግና መንግስት ወደ ሽግግር ይወስደናል የሚል ተስፋ ጨርሶ እንደሌለ አውቃችሁ የጀመራችሁትን እንቅስቃሴ ጠንክራችሁ እንድትቀጥሉበትና ከኦሮሞ ቄሮ ለነፃነት ታጋዮች ጎን በመቆም እንድታበረታቱ መግለፅ እንወዳለን::
ድል ለኦሮሞ ህዝብ!
ዘመኑ የጨቋኝ ስርዓት ማክተሚያ ጊዜ ነው!
የኦሮሞ ቄሮ ለነፃነት
ሐምሌ 6 ቀን 2020 ዓ.ም.