Tuesday, September 6, 2016

#OromoProtests

ምን ሊቀርብኝ ሁሉን አየውት፣
ይሄ ነው የምልበት ታሬኬን የማወራበት፣
ቀን አሁን አደለም ሁሉንም አየውት።
ተጭኖብኝ የህይወት ድህነት፣
ሳልፈልገው ያለነፃነት ሃብት፣
ሁሉም ቀርቶብኝ ያ ልጅ ሁኜ የተመኘሁት፣
ነፃነት የት ላግኘው ፈልጊ አጣውት።
ሶስት አስር አመታትን አለፍኩ፣
ለአራት አስር አመታት ተጣደፍኩ።
ደግሜ ላስቁጥር አምስት አስር አምታት፣
ቅሊንጦ ገብቼ እስክቃጠል በህይወት፣
ሁሉንም እሞክራለሁ ላጣሁት ነፃነት።
አልጠብቅም በቃ አቃለው ገደቤን፣
ከቤቴ ገብቶል አቁሱሎታል ሆዴን።
አያቴን አጥቼ ስቃጠል ኖሬለው፣
ልጅነት ይዞኝ አፉ ብይሃለው፣
ፍቅር አሽንፋኝ ሁለት ወልጃለው፣
እረስቼው ሳይሆን ይሻልሃል ብይ ነው።
አው ሁሉንም ስምቻለው አይቻለው .
ነፃነት አጥቼ መቶ አመት ከሚሞላኝ፣
በትግሬዋች እጅ እሳት ከሚያቃጥለኝ፣
ያኔ የተቃጠሉ ተብሎ ፀሎት ከምታቀርብልኝ፣
ጀርመን እንደ ዩዳን አመቴን ከምታከብርልኝ፣
እኔም ልጠይቅ ከዘሬ ትግሬ ከተቀላቀለብኝ።
በቅሊንጦ ላጣዋቸው ወገኑቼ ጂጂ ነጋሽ

No comments: