መፍረስ?
======
ለመሆኑ 150 ዓመት ሙሉ አገር እየፈረሰብን፣ ሕግና ሥርዓት እየፈረሰብን፣ ዕምነትና ልማድ እየተናደብን፣ ታሪክና ማንነት እየተሻረብን፣ ቤትና ቤተሰብ እየፈረሰብን፣ ሕዝብና ማህበረሰብ እየተደረመሰብን፣ ሕይወትና አካል እየጎደለብን፣ ዕለት ዕለት እየተገደልን ለኖርን ለእኛ፣ መብት ሲጠየቅ "ትፈርሳለች" የምትባለዋ አገር እንደምን ያለች ናት?
ወንድሜ፣ ያንተዋ ኢትዮጵያ የፈረሰችውስ፣ እኛ መብትና ፍትህ ስለጠየቅን ሳይሆን፣ የእኛን መብት በመግፋት፣ የእኛን የሕዝቦቿን ሰብዓዊ ክብር በመርገጥ፣ እኛን ለማፍረስ ተማምላ ከቤት የወጣች ዕለት ነው።
አብይና የወንጀለኛ ስብስብ የሆነው የብልጥግና 'መንግሥቱም' የፈረሱት፣ እኛን በማፍረስ "ኢትዮጵያን [ከእኛ ከሕዝቦቿ፣ በተለይ ከኦሮሞ] ለመታደግ" በሚል የእብድ መፈክር ዙሪያ መማማል የጀመረ ዕለት ነው።
እና መብት ስለተጠየቀ የሚፈርስ አገር የለም።
የመብትና የፍትህ ጥያቄ የሚያፈርሰው 'አገር' ከሆነም፣ ድሮም አገር አልነበረም ማለት ነው። የመብትና የፍትህ ጥያቄን የማይቋቋምና የማይመልስ፣ አልፎም የሚፈራ አገር፣ አገር ሊባል የተገባ አይደለምና መኖርም የለበትም።
አገር ምድር አይደለም። አገር ፖለቲካዊ ማህበረሰብ ነው። መብቶችንና ጥቅሞችን አሰባስቦ፣ አስማምቶ፣ አቻችሎ በጋራ የሚተዳደር፣ ሥርዓትና ተቋማት ያለው ነገር (entity) ነው። ለዚህ ነው "አገር ማለት ሕዝብ ነው፣ አገር ማለት ሰዉ ነው" የሚባለው።
ሰው እያፈረስክ የምትገነባውም ሆነ የምታድነው አገር የለም።
አንድ ሰው ስትገድል፣ የአንድ ዜጋን መብት አላግባብ ስትጥስ፣ አገራዊ መርሆዎችንና እሴቶችን ስታንኳስስ፣ ያኔ ነው አገር ማፍረስ የጀመርከው።
ሕዝብን ስታፈርስ፣ ወይም ለማፍረስ አቅደህ ላይ ታች እያልክ ስትንከላወስ፣ ያኔ ነው እንደ አገር የፈረስከው።
የሕዝብን ሰብዓዊ ክብር ስታዋርድ፣ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ለመስደብ ተደራጅተህ በሚዲያ ደቦ ተቧድነህ ለፕሮፓጋንዳ የሚሆን የሥራ ክፍፍል አድርገህ ስትዘምት፣ ያኔ ነው እንደ አንድ ፖለቲካዊ ማሕበረሰብ አገራዊ ቁመናህን ያጣኸው።
That's why we say #Abiy_is_the_past, and Ethiopia is the home that never was for us. And that's why we say...
#Abiy_must_be_removed!
#ለእነ_መፍረስ_ብርቁ #ለእነ_አፍራሽ!
No comments:
Post a Comment