Monday, August 8, 2016

#OromoProtests

ስለ ጀግንነታቸው ምስክር ነኝ 
=================
Via Abuki Abuki
በዕለተ ቅዳሜ አብዮት አደባበይ በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ፌደራሎቹ ሰልፈኛውን ግማሹን አስረው ግማሹን ደብድበው ካበተኑ በኃላ መንገድ ላይ የሚመላለሰውን ወጣት አስገድደው መታወቂያውን ማየት ጀመሩ፡፡ የአዲስ አበበ መታወቂያ የያዘውን እየለቀቁ የኦሮሚያ ክልል መታወቂያ ያያዘውን ደግሞ ማሰር ጀመሩ፡፡ የኦሮሚያ መታወቂያ የያዙትን ሁከት ልትፈጥሩ ነው እዚህ ድረስ የመጣችሁት፣ ዋጋችሁን ነው የምንሰጣችሁ እያሉ ያስፈራሯቸውም ነበር፡፡ ታሳሪዎችን ጫማዎቻቸውን እያሰወለቁ በባዶ እግረራቸው ወደ ትንሿ ሜደ እየደበደቡ ወሰዷቸው፡፡ የሚገርመው ፖሊሶቹ እየደበደቡ ወደ ትንሿ ሜዳ በሚወስዷቸው ወክት የተወሰኑት ወጣቶች እጃቸውን በማቆላለፍ ከፍ አርገው ተቃውሟቸውን ሲገልጹ ነበር፡፡ 
.
.
በመካከል አንዱን ወጣት ሊያልፍ ሲል በቁጣ ስሜት ጠሩትና መታወቂያውን እንዲያሳያቸው ሲጠይቁት ወጣቱ የወዛ አልነበረምና "ከእትዮጵያዊነት በላይ ምን መታወቂያ አለኝ? እትዮጵያዊ መሆኔን እንደሆነ ሌላ ማረጋጋጫ ሳያስፈልጋችሁ ገፅታዬን ብቻ አይታችሁ መፍረድ ትችላላችሁ" አላቸው፡፡ ይሄን አንዱ ፌደራል በያዘው ቆምጥ ሁለቴ ከወረደበት በኃላ በድጋሚ መታወቂያውን እንዲያሳይ ጠየቀው ...."ወጣቱ ግን ከአቋሙ ውልፍት አላለም፡፡ "ለእኔ ከእትዮጵያዊነት ሌላ መታወቂያ የለኝም፡፡ እትዮጵያዊነቴ ካሳሰረኝ ከፈለጋችሁ እሰሩኝ" ሲል ተሟገታቸው፡፡ እትዮጵያዊነት የምይገባቸው ርህራዬ ያልፈጠረባቸው ፌደራሎችም ወጣቱን እስኪበቃቸው ደብድበው ፒክፕ መኪና ላይ አፈናጠው ወሰዱት፡፡ እንግዲህ ፖሊስ ጣቢያ አድርሰው እንዴት ሊያሰቃዩት እንደሚችሉ መገመቱ ቀላል ነው፡፡ ፈጣሪ ብርታቱን ይስጠው! ......የወጣቱ ፅናት gin የሚገርም ነበር፡፡ ከእትዮጵያዊነት ሌላ መታወቂያ እንደሌለው ሲናገር በ ራስ መተማመንና በኩራት ስሜት ነበር፡፡
.
.
በዚሁ አጋጣሚ ከኦሮሚያ የመጡት ወጣቶች ጀግና ለመሆናቸው ቁጥር አንድ ምስክር ነኝ፡፡ ለደቂቃዎችም ቢሆን በዛ ሁላ አውሬ ሰራዊት ተከበው የያዙትን ባነርና ባንዲራ ከፍ አርገው ሲያውለበልቡና እጃቸውን በማቆላለፍ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ነበር፡፡ ታዲያ ፍርሃት ሳያሸንፋቸው በድፍረት ተቃውሟቸውን ማሰማታቸው ጀግና ናቸው አያስብልም ትላላችሁ ?

No comments: