Sunday, August 21, 2016

#OromoProtests

ኦሮሞነት ያሳስራል ያስገድላል!
≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈
በአዲስ አበባ ዛሬ ነሐሴ 15 ሊካሄድ የታሰበውን ሰልፍ ተከትሎ ከተማዋ በመለዮ ለባሽ ፌድራል ፖሊስና የአጋዚ ወታደር እንዲሁም ሲቪል በለበሱ ጆሮ ጠቢዎች በወረራ ተይዛ ነበር።
በመስቀል አደባባይ አካባቢ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ወጣቶችን ፌድራሎቹ እያዋከቡ በቀይ ሽበር ሰማዕታት ሀውልት ስር ከአንድ ሰዓት በላይ አግተዋቸው አስጨናቂ ምርመራ በጅምላ ዱላንም ጨምረው ከአካሄዱባቸው በኋላ ሌሎቹን ሲለቁ ‪#‎ዘጠኝ‬ ወጣቶችን በፒካፕ ጭነው ወደ አልታወቀ ስፍራ ወስደዋቸዋል።
በፒካፑ ላይ ብዛት ያለው የተለያየ እግር ጫማ ተከማችቶበት እንደነበር ከዓይን ምስክሮች ለመረዳት ተችሎዋል።
የነዚህ ዘጠኝ ወጣቶች ከሌሎቹ የተለየ ሆኖ የተገኘባቸው ጥፋት መታወቂያቸው ላይ ብሔር የሚለው ቦታ ላይ ‪#‎ኦሮሞ‬ የሚል መገኘቱ ነው።
የአዲስ አበባ ልጅ እንኳን ብትሆን ከኦሮሞ ብሔረሰብ በመወለድህ ብቻ በወንበዴው ስርዓት በማንነትህ ላይ የታወጀው የዘር ማፅዳት ዘመቻ ተቋዳሽ መሆንህ እንደማይቀር ይህ ምልክት ነው።
ታፍሰው ከተወሰዱት ወጣቶች ውስጥ ይደረግባቸው በነበረው ምርመራ ወቅት ለማወቅ እንደተቻለው ሁለቱ የማስተርስ ምሩቅ ሲሆኑ አራቱ የመጀመሪያ ድግሪ ተመራቂዎች ናቸው።
ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ ብዙዎች ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ እስር ቤቱን እንዲሞሉት ተፈርዶባቸዋል።
ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ ብዙዎች ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ የደረሱበት ሳይታወቅ እንዲሁም በየቦታው ተገለዋል። ለዚህም የወደቁባቸው ጎዳናዎች እንዲሁም ሸለቆዎችና ጥሻዎች ድምፅ አውጥተው ይመሰክራሉ።

No comments: