Friday, July 31, 2020

#AbiyMustGo#Ethiopia

ኦሮምያ ላይ ጦርነት ታውጇል። የኦሮሞ ህዝብ መሪዎች ባልፈጸሙት ወንጀል ታስረው ስቃይ ላይ ናቸው። ኦሮሞነት ወንጀል ሆኖ እያሳሰረ ባለበት ዘመን ላይ ነን። ይህ ኦሮሞና ኦሮሞነትን "ምን ታመጣለህ" ባለ መንግስት ላይ የኦሮሞ ህዝብ ምን ማምጣት እንደሚችል ለማሳየት ተገዷል። ኣላማችን ማን ኛውንም ወንድም ብሄር ብሄረሰብ መጉዳት ሳይሆን ይህንን ጸረ ኦሮሞ መንግስት ማንበርከክ ነው። 

ስለሆነም ከሰኞ ሃምሌ 27, 2012 ጀምሮ በመላው ኦሮምያ ኣጠቃላይ የመንገድ መዝጋትና የኢኮኖሚ ኣድማ ይጀመራል። በዚህም መሰረት ማንኛውም ተሽከርካሪ ከሌሎች ክልሎች ኦሮምያን ኣቋርጦ ወደ ሸገር ኣይገባም ኣይወጣም። ይህንን ዕቀባ ተላልፎ ለመንቀሳቀስ የሚሞክር በማንኛውም ቦታና ሁኔታ ችግር ሊደርስበት ስለሚችል ቄሮ ኣስቀድሞ ያስጠነቅቃል።
Mohammed Adem 
Eid Mubarak

No comments: