Friday, July 24, 2020

#AbiyMustGo#Ethiopia

የአቶ ጀዋር መሀመድ: አቶ በቀለ ገርባ: ሀምዛ ቦረና; እና የአቶ ሸምሰድን ጣሃ አያያዝ የሰብአዊ መብቶቻቸውን የሚጥስ ነው።

ሀ . ጭካኔ የተሞላበት፤ ኢሰብአዊ የሆኑ ወይም ሰብአዊ ክብርን የሚያዋርዱ አያያዞች

1. ስማቸው ከላይ የተጠቀሰው ተጠርጣሪዎች በኢፌዲሪ ፖሊስ ኮሚሽን የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ይገኛሉ። ክፍላቸው በ24 ሰዓት ዉስጥ ከሁለት ጊዜ በላይ አይከፈትም፡፡ እንደተዘጋባቸው መሽቶ ይነጋል፡፡ክፍሉ የተፈጥሮ የፀሐይ ብርሃን የማያስገባ ጨለማ ከመሆኑ የተነሳ በአይናቸው ላይ ከፍተኛ የጤና ችግር አስከትሏል፡የክፍሉ መስኮት ለምልክት ብቻ የተቀመጠ እንጂ በበቂ ሁኔታ ንፁህ አየር ስለማያስገባ በተለይ ጧት ጧት ከእንቅልፉ ሲነሳ ራሱን የማይታመም የለም፡፡ ፡
2. በተለይ አቶ ጀዋር መሀመድ: እና አቶ በቀለ ገርባ: ለየብቻቸው ነው የታሰሩት። Solitary confinement is the isolation of detainees for long hours or more a day without any meaningful human contact.They have the right to be free of cruel and unusual punishment of which solitary confinement violates those rights.
2. በኢፌዲሪ ፖሊስ ኮሚሽን የፌዴራል ወንጀል ምርመራ አስተዳደር ምግብ ለማቀበል ብቻ በሩን ስለሚከፈት በሕጉና በደንቡ መሠረት አቤቱታ ማቅረቢያ ሁኔታ የለም፡፡ 
3. የቴሌቪዢን እና የቤተ መፅሐፍት አገልግሎት የሉም፡፡
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ሁኔታዎች ካሉ አለም አቀፍ የሰዎች ጭካኔ በተሞላበት፤ኢሰብአዊ ከሆነ ወይም ክብርን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት መግለጫ (Convention against Torture or Other Cruel, Inhuman or Degrading Treatment or punishment) መሠረት በኢፌዲሪ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ መዕከል የተጠርጣሪዎች አያያዝ ጭካኔ የተሞላበት፤ ኢሰብአዊ የሆነ ወይም ሰብአዊ ክብራቸውን የሚያዋርድ አያያዝ ነዉ፡፡ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚቴ (UNHRC) ያስቀመጠዉ ጭካኔ የተሞላበት፤ኢሰብአዊ የሆነ ወይም ሰብአዊ ክብርን የሚያዋርድ አያያዝ ልተረጎም የሚገባበትን አግባብ ይህንኑ የሚያጠናክር ነዉ፡፡
ኢትዮጵያ ባፀደቀቻቸዉ አለም አቀፋዊና አህጉራዊ የሰብአዊ መብት ሰነዶች ዉስጥ ፡- በሁሉን አቀፍ ሰበአዊ መብቶች መግለጫ (UDHR) አንቀፅ 5 ፣በአለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል-ኪዳን (ICCPR) አንቀፅ 7 እና 10፣ በአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች መብት ቻርተር አንቀፅ 5 ሥር እነዚህ ጭካኔ የተሞላበት፤ ኢሰብአዊ የሆኑ ወይም ሰብአዊ ክብርን የሚያዋርዱ አያያዞች በቅጣት መልክም ቢሆን በእስረኞች ላይ መጠቀም በጥብቅ የተከለከለ ነዉ፡፡ 
በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 9(4) መሠረት እነዚህ አለም አቀፍ ስምምነቶች የኢትዮጵያ ሕግ አካል ናቸዉ፡፡ የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 21(1) እና 18 ሥርም ይህ ክልከላ በተመሳሳይ መልኩ ተደንግጓል፡፡ 
ከላይ የዘረዘርናቸዉ የኢፌዲሪ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ መዕከል በተጠርጣሪዎች ላይ የወሰደዉ እርምጃዎች እነዚህን የኢት/ያ ሕግ አካል የሆኑትን አለም አቀፍና አህጉራዊ ሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን በግልፅ የሚጥሱ ናቸዉ፡፡ 
ከሁሉም በላይ ደግሞ የሕጎች ሁሉ የበላይ ከሆነዉ ሕገመንግስት (አንቀፅ 9(1)) ጋር በቀጥታ የሚጋጩ ድርጊቶች ናቸዉ፡፡ በመሆኑ እነዚህ ማዕከሉ በተጠርጣሪዎች ላይ የፈፀማቸዉ ድርጊቶች ኢ-ሕ/መንግስታዊ ናቸዉ።
የተባበሩት መንግስታት የእስረኞችን አያያዝ በተመለከተ አለም አቀፍ ዝቅተኛ መመዘኛዎችን (The Standard Minimum Rules for the Treatment of Prisoners) አስቀምጧል፡፡ በእነዚህ መመዘኛዎች መሠረት የእስረኞች መኖሪያ ክፍሎች አጠቃላይ የጤና መመዘኛዎችን በተለይም፣የአከባቢዉን የአየር ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ፤እና የሚይዙት የአየር መጠን፤የስፋት፤ የመብረትና የሙቀት ሁኔታ የሚያሟል መሆን አለባቸዉ፡፡ ታራሚዎች በቀን ቢያንስ ለተወሰኑት ሰዓታት መናፈስ አለባቸዉ፡፡ አቤቱታ ለማቅረብ የሚያስችል ሥርዓትና የተመቻቸ ሁኔታ መኖር አለበት፡፡ እነዚህ መመዘኛዎች ብሔራዊ ሕጎቻችን ዉስጥም ተካተዉ እናገኛቸዋለን፡፡ በፌ/ማ/ቤ/ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ. 365/99 አንቀፅ 22 እና 26 መሠረት እስረኞች ሰብአዊ ክብራቸዉ ተጠብቆ መያዝ አለባቸዉ፤ መኖሪያ ቦታቸዉ ለጤና ጠንቅ ያልሆነ፤ በቂ ንፁህ አየርና ብርሃን ያለዉ መሆን አለበት፡፡ የፌ/ታራሚዎች አያያዝ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁ.138/99 አንቀፅ 6 መሠረትም ታራሚዎች የሚኖሩባቸዉ ክፍሎች መፅሐፍ ለማንበብ የሚያስችል በቂ ብርሃንና ለጤንነት ተስማሚ አየር የሚያስገቡ መስኮቶች እና በሌሊት መፅሐፍ ለማንበብ የሚያስችል የአይንን ጤንነት የማይጎዳ መብራት ያላቸዉ መሆን ይኖሩባቸዋል፡፡ 
በመሆኑም የኢፌዲሪ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ መዕከል በተጠርጣሪዎች ላይ የፈፀማቸዉ ድርጊቶች እነዚህን አለም አቀፋዊ እና በአገራችን ሕጎች ዉስጥ የተቀመጡ ሕጋዊ ብሔራዊ ዝቅተኛ መመዘኛዎችን የሚጥስ ነዉ፡፡ 

ለ.ከቅርብ ዘመዶቻቸዉ፤ ከጓደኞቻቸዉ …..ወዘተ ጋር የመገናኘት መብት
ተጠርጣሪዎች ልጠይቋቸዉ የሚችሉትን የቤተሰብ አባላት ዝርዝር አምጡ ተብለዉ የሕገ መንግስት አንቀፅ 21(2) መሠረት ከቅርብ ዘመዶቻቸዉ፤ ከጓደኞቻቸዉ …..ወዘተ ጋር የመገናኘት መብት አለን በማለት በመከራከራቸዉ ምግብ ከሚያመጣላቸዉ የቤተሰብ አባል ዉጪ ፤ከዚህ ከቤተሰብ አባል ጋር ከሚመጡ ዘመዶቻቸዉ ጋር መገናኘት አይችሉም፡፡ ከቤተሰብ አባሉ ጋር እራሱ ከአምስት ደቂቃ በላይ መነጋገር አይፈቀድላቸዉም፡
ከቤተሰብ አባሉ ጋር እራሱ ከ25-40 ሜትር ርቀት ላይ ሆኖ እንድነጋገሩ የተገደዱ ቢሆንም ከአምስት ደቂቃ በላይ መነጋገር አይፈቀድለትም፡፡ ይህ የአምስት ደቂቃ ገደብ ሕጋዊና ሕገመንግስታዊ መሠረት ያሌለዉ ከመሆኑም በላይ ተጠርጣሪዎች የቤተሰብ አስተዳዳሪ በመሆናቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመወያየት የሚያሳልፉት ቤተሰባዊ ዉሳኔዎች ከመኖራቸዉ አንፃር ሲታይ ከጠያቂ ቤተሰቦቹና ዘመዶቹ ጋር ያለዉ ቆይታ በዚህ መልኩ መገደቡ ኢፍትሃዊ ነዉ፡፡

No comments: