Monday, August 3, 2020

#AbiyMustGo#Ethiopia

ህዝብን ማሸነፍ የሚችል ሀይል የለም!  እራስን ማታለል (self-deception)  ውስጥ ገብተን ካልሆነ በስተቀር 50  ሚሊዮን የኦሮሞ ህዝብ (በብዛት) የብልጽግናውን መንግስት እንዳልተቀበለው ግልጽ ነው።ህዝብን ሰብሮ የምናልማትን "nation-state" አሁን ያለው መንግስት ይገነባልናል ብለው የሚያስቡ ከታሪክ ቆም ብለው ቢማሩ መልካም ነበር።አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ ችግር ዘላቂ መፍትሄ የሚያገኘው ቁጭ ብሎ በመነጋገር እና ፖለቲካዊ መፍትሄ በመፈለግ ነው።  በፍለጠው ቁረጠው፣  ልጣቸው ተርሶ ጉድጓዳቸው ተምሶም አእምሮዋቸው ካልበሰለ የደርግ ወታደሮች በሚሰነዘር አጥፊ ምክር እንዲሁም አንድን ህዝብ demonize በማድረግ ላይ ባተኮረ የሚዲያ ደቦ ከገባንበት ውጥንቅጥ ውስጥ አንወጣም። 

አይደለም እንደ ኢትዮጵያ ያለች የደቀቀ ኢኮኖሚ፣ የተከፋፈለ ህዝብ፣ እዚ ግባ የማይባል የወታደራዊ አቅም ያላት ሀገር ቀርቶ ከልእለ ሀያልዋ አሜሪካ በመቀጠል  በወታደራዊ ጡንቻዋ ተገዳዳሪ የሌላት እንዲሁም ትልቅ የህዝብ ቁጥር ያላት ራሺያ ከአንድ ሚሊየን ብዙም ያልዘለለ የህዝብ ቁጥር ያለውን (ነገር ግን እምቢ ያለውን) የቺቺኒያ ህዝብ ለማንበርከክ ምን ያህል እንደተሳናት የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። እምቢ ያለውን የቺቺኒያ ህዝብ የአዳፍኔ፣ የሞርታር፣ የ BM ፣ የታንክ የእሳት ቁጣን የሚተፉ ላንቃዎች እንዲሁም ከዘመናዊዎቹ  "SU ጦር አውሮፕላኖች እና  Mi ሄሊኮፕተሮች የሚወርድ የቦምብ እና የተምዘግዛጊ ሚሳኤል ውርጅብኝ ሊያንበረክኩት አልቻሉም። በጦርነቱ  ራሺያ ላይ የደረሰው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የሞራል፣ እና ወታደራዊ ኪሳራ እጅግ አስከፊ ነበር። ቺቺኒያ አሁን እራስ ገዝ የሆነ በራሺያ ፌደሬሽን ውስጥ የሚገኝ ሪፐብሊክ ነው። 

ጠንካራ የአላማ መሰረት ላይ የተገነባ ትግል በተከፋይ ወታደሮች አፈሙዝ ፊት አይሽመደመድም!!

No comments: